Home > Trip Types > ኢየሩሳሌም

ኢየሩሳሌም

If you want to download the package click ፋሲካ – Fasika  or  ደብረዘይት – DebreZeit 

የ2011 ዓ.ም. የደብረዘይት በዓል ጉብኝት መርሐ ግብር

አንደኛ ቀን፡ አርብ መጋቢት 20/ማርች 29

ተጓዦች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ጉዞ ወደ ቴል አቪቭ ያደርጋሉ፣ አመሻሽ ላይ ቴል አቪቭ ይደርሱና አስፈላጊውን የኢሜግሬሽን ሥርዓት ፈፅመው በተዘጋጁት አውቶብሶች ውስጥ ሆነው ወደ ኢየሩሳሌም ያቀናሉ፣ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ የሆቴል ክፍሎቻቸውን ይረከባሉ፡፡ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።
ሁለተኛ ቀንቅዳሜ መጋቢት 21/ማርች 30

ተጓዦች ቁርስ ከተመገቡ በኋላ ከቤተ ሳይዳን ጉብኝቱን በመጀመር ጌታ የተሰቀለበትን ቀራንዮን፣ የቀብሩን ቦታ ጎለጎታን ጨምሮ አሥራ አራቱን ፍኖተ መስቀሎች፣ ንግሥት እሌኒ ያሠራችውን ቤተ ክርስቲያን ይጎበኛሉ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የዴር ሱልጣን ገዳም ፀሎት ያደርጋሉ፣ የምሳ ዕረፍት ያደርጋሉ፣ በመቀጠል የእርገቱን ቦታ፣ አባታችን ሆይ ያስተማረበትን ቦታ፣ ጌቴሰማኒ  ታችን የጸለየበትን አጸደ ሐምል /የአታክልቱን ቦታ/፣ የእመቤታችን የማርያምን መቃብር እና በክብር ያረገችበትን /ፍልሰታ ማርያም/ ቦታ፣ የዳዊት መቃብርን ይጎበኛሉ፣ እረፍት ያደርጋሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።
ሶስተኛ ቀን፡ እሁድ መጋቢት 22/ማርች 31

በለሊት ወደ ደብረገነት ኪዳነምህረት ገዳም ለስርዓተ ቅዳሴ ይሄዳሉ፣ ወደ ሆቴላቸው ተመልሰው ቁርስ ተመገበው እስከ እኩለ ቀን እረፍት ያደረጋሉ፣ ከዚያም ምሳ ይመገባሉ፣ ወደ ቤቴልሔም በማቅናት ጌታችን የተወለደበትን፣ የእረኞቹን መንደር ይጎበኛሉ፣ መጨረሻም ወደ ሆቴላቸው ተመልሰው ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።
አራተኛ ቀን፡ ሰኞ መጋቢት 23/ኤፕሪል 01

ተጓዦች ቁርስ ከተመገቡ በኋላ የኢየሩሳሌም ሆቴል ክፍሎቻቸውን አስረክበው ወደ ኢያሪኮ በማቅናት ገዳመ ቆረንጦስን፣ የኤልሣ ምንጭን፣ የዘኬዎስ ዛፍን ይጎበኛሉ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የኢያሪኮ ገብርኤል ገዳም ፀሎት ያደርጉና የምሳ እረፍት ያደርጋሉ፣ የሙት ባሕርን ጨምሮ ቁምራንና አካባቢውን ይጎበኛሉ፣ ከዚያም ወደ ጥብርያዶስ/ገሊላ ባህር ያቀናሉ፣ የሆቴል ክፍሎቻቸውን ረከባሉ፣ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም በገሊላ ባህር አቅራቢያ በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።
አምስተኛ ቀን፡ ማክሰኞ መጋቢት 24/ኤፕሪል 02

ተጓዦች በጠዋት ተነስተው በዮርዳኖስ ወንዝ ይጠመቃሉ፣ ከቁርስ በኋላ የጀልባ ጉዞ በገሊላ ባህር ላይ ያደርጋሉ፣ የአንቀፀ ብፁዓን ስብከት ተራራን፣ ጌታ 3 አሳና 5 እንጀራ አበርክቶ ያበላበትን ቅዱስ ስፍራ ይጎበኙና በገሊላ ባህር አጠገብ ምሳ ይመገባሉ፣ ብርያዶስን፣ ቅፍርናሆምን ጎብኝተው ወደ ሆቴል ይመለሳሉ፣ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም በገሊላ ባህር አቅራቢያ በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።
ስድስተኛ ቀን፡ ረቡዕ መጋቢት 25/ኤፕሪል 03

በጠዋት ተጓዦች ቁርስ ከተመገቡ በኋላ ደብረ ታቦርን፣ ናዝሬትንና ቃና ዘገሊላን ጎብኝተው የምሳ ዕረፍት ያደርጋሉ፣ ብስራተ ብኤልንና የእመቤታችንን ምንጭ ጨምሮ የአካባቢውን አብያተ ክርስቲያናት ጎበኝተው የመልስ ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም ያደርጋሉ፣ ሆቴል ክፍሎቻቸውን ተረክበው ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም በገሊላ ባህር አቅራቢያ በሚገኘው ሆቴል ይሆናል፡፡
ሰባተኛ ቀን፡ ሐሙስ መጋቢት 26/ኤፕሪል 04

ተጓዦች በሆቴል ቁርስ ከተመገቡ በኋላ ኤማሁስን እና አይነ ከርምን ይጎበኙና የምሳ ዕረፍት ያደርጋሉ፣ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው የዕረፍትና የስጦታ እቃዎች የሚገዙበት ጊዜ ይሆናል፣ ለመልስ ጉዞ ዝግጅት ያደርጋሉ፣ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።
ስምንተኛ ቀን፡ አርብ መጋቢት 27/ኤፕሪል 05

በሆቴል ቁርስ ይመገባሉ፣ ከዚያም የሆቴል ክፍሎችን አስረክበው በተዘጋጀላቸው አውቶቢስ በመሆን ወደ አየር ማረፊያ ይጓዛሉ። ተጓዦች ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ይደርሳሉ

ማስታወሻ፡- ይህ የጉብኝት ፕሮግራም በጊዜያዊነት የተያዘ ሲሆን፣ በጉብኝቱ ወቅት በሚጎበኙ ቦታዎች በሚኖሩ ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ በመመርኮዝ መጠነኛ ለውጦች ሊያደረግበት ይችላል፣ ይህንንም በወቅቱ ለተጓዥ ምዕመናን የምናሳውቅ ይሆናል::
የዋጋ ዝርዝር፣
1. የደርሶ መልስ የበረራ ትኬት (አዲስ-ቴልአቪቭ-አዲስ)፣ ቪዛ፣ የጉዞ ኢንሹራንስና የመመዝገቢያ 000.00 ብር፣
2. በኢየሩሳም የጉብኝት አገልግሎት ዋጋ በሰው 000.00 ዶላር በአንድ ሰው፣ በጉብኝት ፓኬጅ ዋጋው የተካተቱ፡- ደረጃ የጠበቁ ባለ4 ኮከብ የማረፊያ ሆቴሎች፣ ቁርስ፣ ምሳ፣ እራት፣ የዘመናዊ አውቶቢስ መጓጓዣ ትራንስፖርት፣ የስብከተ ወንጌል መምህርና አስጎብኚዎች፣ የሚጎበኙ ቦታዎች የመግቢያ ክፍያ፣ የመጠመቂያ ልብስ፣ የፀበል መቅጃ ኮዳ፣
3. በፓኬጅ ዋጋው ያልተካተተ፡- የአስጎብኚዎችና የሹፌሮች ጉርሻ/ቲፕ፣

የ2011 ዓ.ም. የልደት በዓል የጉብኝት መርሐ ግብር

አንደኛ ቀን፡ ቅዳሜ ታህሳስ 27 2011 ዓ.ም./ጃንዋሪ 5 2019
ተጓዦች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ጉዞ ወደ ቴል አቪቭ ያደርጋሉ፣ አመሻሽ ላይ ቴል አቪቭ ይደርሱና ስፈላጊውን የኢሜግሬሽን ሥርዓት ፈፅመው በተዘጋጁት አውቶብሶች ውስጥ ሆነው ወደ ኢየሩሳሌም ያቀናሉ፣ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ የሆቴል ክፍሎቻቸውን ይረከባሉ፡፡ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።
ሁለተኛ ቀን፡ እሁድ ታህሳስ 28 2011 ዓ.ም./ጃንዋሪ 6 2019
በዚህ ቀን በተያዘው የጉብኝት መርሃ ግብር መሰረት ተጓዥ ምእመናን ከቤተ ሳይዳ ጉብኝታቸውን በመጀመር ለ38 ዓመት በአልጋ ላይ የነበረዉ መጻጉ ወደ ተፈወሰበት ቦታ በመሄድ የመጠመቂያውን ቦታ እና በቅድስት ሐና ስም የታነጸውን ቤተመቅደስ ይጎብኛሉ፣
የአሥራ አራቱን ፍኖተ መስቀሎች ጉብኝት እስከ ዘጠነኛው ምዕራፍ ድረስ ማብራሪያና ትምህርት እየተሰጣቸው ጎብኝተው በመቀጠልም ጌታ የተገነዘበትን፣ የተሰቀለበትን (ቀራንዮ)፣ የተቀበረበትን ቦታ (ጎለጎታ) ይሳለማሉ፣ የምሳ እረፍት ያደርጋሉ፣
በመቀጠል ወደ ሆቴላቸው ተመልሰው ዕረፍትና ለማታ ፀሎት ዝግጅት ያደርጋሉ፣ ወደ ቤቴልሄም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኢየሱስ ገዳም ለፀሎት ይሄዳሉ፣ ስርዓተ ቅዳሴ ሲያበቃ ወደ ሆቴል ተመልሰው እረፍት ያለፍጋሉ፣
አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።
ሶስተኛ ቀን፡ ሰኞ ታህሳስ 29 2011 ዓ.ም./ጃንዋሪ 7 2019
ተጓዦች በሆቴል ቁርስ ተመገበው እስከ እኩለ ቀን እረፍት ያደረጋሉ፣ ከዚያም ምሳ ይመገባሉ፣ ከሆቴላቸው በመውጣት መጀመሪያ ጌታ በሐዋርያት መካከል በክብር ወደ ሰማይ ያረገበትን ቅዱስ ስፍራ፣ ከዚያም ሐዋሪያቶች ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት ብለው እንዲጸልዩ በጠየቁት መሰረት አባታችን ሆይ የሚለውን ጸሎት ያስተማረበትን ቅዱስ ስፍራና ጌታ ያድርበት የነበረበትን የኤሌዎንን ዋሻ ይጎበኛሉ፣ በመቀጠልም ሙሉ የኢየሩሳሌም ከተማን በሚያሳየው ሰበን አርክ አደባባይ በመገኘት ስለጥንቷ የዳዊት ከተማ፣ የሞሪያ ተራራ፣ ጌታ ስለ ኢየሩሳሌም መፍረስ ያለቀሰበትን ቦታ ይጎበኛሉ፣ በመቀጠልም ወደ ጌቴሰማኒ በመውረድ ጌታችን የጸለየበትን የአታክልቱን ቦታ፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የመቃብር እና በክብር ያረገችበትን ቅዱስ ስፍራ ጎብኝተው፣ የዳዊት መቃብርን፣ ቤተ ፋጌን እና ጌታ የመጨረሻ እራት ያበላበትን ቦታዎች ይጎበኛሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።
አራተኛ ቀን፡ ማክሰኞ ታህሳስ 30 2011 ዓ.ም./ጃንዋሪ 8 2019
ይህ ቀን ተጓዦች ኢየሩሳሌምን በመልቀቅ ለሁለት ቀናት በናዝሬትና በአካባቢው የሚቆዩበት ቀን ነው፣ ስለሆነም ጠዋት ከቁርስ በኋላ የኢየሩሳሌም ሆቴል ክፍሎቻቸውን አስረክበው ጉዞ ወደ ጥብርያዶስ ያደርጋሉ፣ በመንገዳቸው ላይም በኢያሪኮ በመገኘት በተራራ  ናት ላይ የሚገኘውንና ጌታ አርባ ቀን አርባ ለሊት የፆመበትንና የፀለየበትን ገዳመ ቆረንጦስን ይሳለማሉ፣ ከዚያም የኤልሣ ምንጭን ጎብኝተውንና ፀበል ተረጭተው ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የኢያሪኮ ገብርኤል ገዳም በማቅናት ፀሎት ያደርጋሉ፣ ከዚያም  ዘኬዎስ ዛፍን ተመልክተው የምሳ እረፍት ያደርጋሉ፣ የሙት ባሕርንና አካባቢውን ጎብኝተው ወደ ናዝሬት በማቅናት እዚያም ሲደርሱ  ሆቴል ማረፊያ ክፍሎቻቸውን ይረከቡና እረፍት ያደርጋሉ፣ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም ናዝሬት በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።
አምስተኛ ቀን፡ ረቡዕ ጥር 1 2011 ዓ.ም./ጃንዋሪ 9 2019
ተጓዦች በጠዋት ተነስተው የተዘጋጀላቸውን የመጠመቂየ ልብስ ተረክበው በዮርዳኖስ ወንዝ ተምሳሌታዊ ጥምቀት ያደርጋሉ፣ ጉብኝታቸውንም በመቀጠል የአንቀፀ ብፁዓን ስብከት ተራራ ይጎበኛሉ፣ ከዚያም ጌታ 3 አሳና 5 እንጀራ አበርክቶ ያበላበትን ቅዱስ ስፍራ ይጎበኛሉ፣ ወደ ቅፍርናሆም በማቅናት ጌታችን ያስተምርበት የነበረውን የአይሁድ ቤተ ምኩራብ፣ የሐዋርያው የቅዱስ  ጥሮስ፣ የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ፣ የቀራጩ የማቴዎስ ጨምሮ ሌሎችም ሃዋርያት ለአገልግሎት የተጠሩበትን ቦታዎችና ጌታ ይኖርበት የነበረውን የቅፍርናሆም መንደር ፍርስራሽ ይጎበኛሉ፣ በመቀጠልም በገሊላ ባህር አጠገብ ልዩ የአሳ ምሳ ተመግበውና ተምሳሌታዊ የጀልባ ጉዞ በገሊላ ባህር ላይ አድርገው የዕለቱ ጉብኝት ያበቃል፣ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም ናዝሬት በሚገኘው ሆቴል  ሆናል።
ስድስተኛ ቀን፡ ሐሙስ ጥር 2 2011 ዓ.ም./ጃንዋሪ 10 2019
ተጓዦች ምዕመናን ቁርስ በሆቴል ተመግበው የእመቤታችንን ምንጭ ጎብኝተውና ጸበል ቀድተው ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታን እንደምትፀንስ ያበሰራትን ቅዱስ ስፍራ ጎበኝተው ወደ ቃና ዘገሊላ አቅንተው የሰርግ ቤቱን ይጎበኛሉ፣
የምሳ ዕረፍት አድርገው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባህርየ መለኮቱን በገለፀበት የደብረ ታቦር ተራራ ተገኝተውና ፀሎት አድርገው የመልስ ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም ያደርጋሉ፣ የሆቴል ክፍሎቻቸውን ተረክበው ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም በገሊላ ባህር አቅራቢያ በሚገኘው ሆቴል ይሆናል፡፡
ሰባተኛ ቀን፡ አርብ ጥር 3 2011 ዓ.ም./ጃንዋሪ 11 2019፣
ተጓዦች ቁርስ በሆቴል ይመገባሉ፣ በዚህ ቀን ተጓዥ ምዕመናን ወደ ቤቴልሔም በማቅናት ጌታችን የተወለደበትን ዋሻ ከተሳለሙ በኋላ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኢየሱስ ገዳም ፀሎት ያደርጋሉ፣ በመቀጠልም ሄሮድስ ህፃኑን ሊገድል በፈለገ ጊዜ ቅዱስ  ብርኤል ለቅዱስ ዮሴፍና ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ህፃኑን ይዘው እንዲሸሽ እስከነገረው ሰዓት ድረስ የቆዩበትን የወተት ዋሻ  መባል የሚጠራውን ቅዱስ ስፍራ ይጎበኛሉ፣
በመቀጠል የጌታ መልአክ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም እንደተወለደ የምሥራቹን ለእረኞቹ ወደ አበሰረበትና ኖሎት ተብሎ የሚጠራውን የእረኞች መንደር ይጎበኙና የምሳ እረፍት ያደርጋሉ፣
በመቀጠል ወደ አይንከርም በመሄድ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የተወለደበትንና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ኤልሳቤጥን ልትጠይቃት በሄደችበት ጊዜ እመቤታችንና ኤልሳቤጥ ተገናኝተው ሰላምታ የተለዋወጡበትን ገዳም ይጎበኛሉ፣
ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው በመንገዳቸው ላይ ጌታችን ከኤማሁስ መንገደኞች ከሉቃስና ቀልዮጳ ጋር ተገናኝቶ ህብስትን ባርኮ በለባትን ቅዱስ ሥፍራ ይጎበኛሉ፣
ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው የዕረፍትና የስጦታ እቃዎች የሚገዙበት ጊዜ ይሆናል፣ ለመልስ ጉዞ ዝግጅት ያደርጋሉ፣ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።
ስምንተኛ ቀን፡ ቅዳሜ ጥር 4 2011 ዓ.ም./ጃንዋሪ 12 2019፣
በሆቴል ቁርስ ይመገባሉ፣ ከዚያም የሆቴል ክፍሎችን አስረክበው በተዘጋጀላቸው አውቶቢስ በመሆን ወደ አየር ማረፊያ ይጓዛሉ። ተጓዦች ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ይደርሳሉ፣
ማስታወሻ፡- ይህ የጉብኝት ፕሮግራም በጊዜያዊነት የተያዘ ሲሆን፣ በጉብኝቱ ወቅት በሚጎበኙ ቦታዎች በሚኖሩ ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ በመመርኮዝ መጠነኛ ለውጦች ሊያደረግበት ይችላል፣ ይህንንም በወቅቱ ለተጓዥ ምዕመናን የምናሳውቅ ይሆናል::

You can send your enquiry via the form below.

ኢየሩሳሌም