Home > Trip Types > More Than One Night Tour > ትንሳዔ በቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም

ትንሳዔ በቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም

በድል ወደ ቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም የትንሳዔ የጉብኝት ፕሮግራም መረጃ፣

ቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም መንፈሳዊ ጉብኝት፣

ከጥንት ከንግሥተ ሳባ ዘመን ጅምሮ እስከ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ዘመን ድረስ፣ ከዚያም አልፎ እስከ አሁን አባቶቻችን ሲያደርጉ እንደቆዩት ታሪካዊቷን ቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም በመሳለም መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በሥጋ በተገለጠበት ወራት በሔደበት ጎዳና ተመላለሰው፣ የረገጠውን መሬት ረግጠውና ሌሎች መካነ ቅዱሳትን ጎብኝተው ትምህርትና በረከትን አግኝተው ይመለሱ፣

ይህንን ጥንታዊና የተቀደሰ ጉዞ ለመስቀል፣ ለልደት/ለገና፣ ለደብረዘይት፣ ለትንሳዔ፣ ለዕርገት እና ለፍለሰታ በዓላት ባለን ሰፊ ልምድና እውቀት ከልብ ከሆነ አገልግሎት ጋር እርሶም ሆኑ ወላጆችዎ ከእኛ ጋር እንዲጓዙ ግብዣ ስናቀርብልዎ ከታላቅ ደስታ ጋር ነው፣

ለትንሳዔ በዓል የሚደረገው የጉብኝት ፕሮግራሞች 14 ቀናት የሚሸፍን ፕሮግራም ነው፣

Day 1
አንደኛ ቀን፡ ማክሰኞ ሚያዝያ 06 2012 ዓ.ም./ኤፕሪል 14 2020፣

ተጓዦች ከሰዓት በኋላ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ጉዞ ወደ ቴል አቪቭ ያደርጋሉ፣

Day 2
ሁለተኛ ቀን፡ ረቡዕ ሚያዝያ 07 2012 ዓ.ም./ኤፕሪል 15 2020፣

ንጋት ላይ ቴል አቪቭ ይደርሱና አስፈላጊውን የኢሜግሬሽን ሥርዓት ፈፅመው በተዘጋጁት አውቶብሶች ውስጥ ሆነው ወደ ኢየሩሳሌም ያቀናሉ፣ የእርገቱን ቦታ፣ አባታችን ሆይ ያስተማረበትን ቦታ፣ ጌቴሰማኒ ጌታችን የጸለየበትን አጸደ ሐምል /የአታክልቱን ቦታ/፣ የእመቤታችን የማርያምን መቃብር እና በክብር ያረገችበትን /ፍልሰታ ለማርያም/ ቦታ ይጎበኛሉ፣ የምሳ እረፍት ያደርጋሉ፣ ከዚያም የሆቴል ክፍሎቻቸውን ይረከባሉ፣ እረፍት ያደርጋሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።

Day 3
ሶስተኛ ቀን፡ ሐሙስ ሚያዝያ 08 2012 ዓ.ም./ኤፕሪል 16 2020፣

ተጓዦች የዳዊት መቃብርን እና ጌታ የመጨረሻ እራት ያበላበትን ቦታ እንዲሁም ቤተ ፋጌን ይጎበኛሉ፣ እኩለ ቀን ላይ በዴር ሡልጣን ገዳም በሕጽበተ እግሩ መርሐ ግብር ላይ ይገኛሉ፣ በፀሎቱ መጨረሻ ወደ ሆቴላቸው ተመልሰው እራት ይመገባሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።

Day 4
አራተኛ ቀን፡ አርብ ሚያዝያ 09 2012 ዓ.ም./ኤፕሪል 17 2020፣

ተጓዦች ከቤተ ሳይዳ ጉብኝታቸውን በመጀመር አሥራ አራቱን ፍኖተ መስቀሎች ይጎበኛሉ፣ በዚህም ጉብኝት ጌታ የተገነዘበትን፣ የተሰቀለበትን (ቀራንዮ)፣ የተቀበረበትን ቦታ (ጎለጎታ) ያካትታል፣ በዴር ሡልጣን ገዳም የስግደትና ፀሎት ስነስርዓት ይሳተፋሉ፣ ከፀሎት በኋላ ወደ ሆቴላቸው ይመለሳሉ፣ እራት ይመገባሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።

Day 5
አምስተኛ ቀን፡ ቅዳሜ ሚያዝያ 10 2012 ዓ.ም./ኤፕሪል 18 2020፣

ተጓዦች በዴር ሡልጣን ገዳም የቄጤማ ስነ ስርዓትና ፀሎት ፕሮግራም ላይ ይሳተፋሉ፣ ኤማሁስን እና አይነ ከርምን ይጎበኙና ወደ ሆቴል ተመልሰው ዕረፍት ያደርጋሉ፣ ከቀኑ 10 ሰዓት ወደ ዴር ሡልጣን ገዳም/ኪዳነ ምህረት የኢትዮጵያ ቤ/ክርስትያን ይሄዳሉ፣ ከፀሎት በኃላ የመፈሰኪያ እራት ተመግበው ወደ ሆቴላቸው ይመለሳሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።

Day 6
ስድስተኛ ቀን፡ እሁድ ሚያዝያ 11 2012 ዓ.ም./ኤፕሪል 19 2020፣

ተጓዦች ቁርስ በሆቴል ይመገባሉ፣ እስከ እኩለ ቀን እረፍት ያደረጋሉ፣ ከዚያም ልዩ የበዓል ምሳ ይመገባሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።

Day 7
ሰባተኛ ቀን፡ ሰኞ ሚያዝያ 12 2012 ዓ.ም./ኤፕሪል 20 2020፣

ተጓዦች ቁርስ በሆቴል ይመገባሉ፣ ወደ ቤቴልሔም በማቅናት ጌታችን የተወለደበትን፣ የእረኞቹን መንደር ይጎበኛሉ፣ በመጨረሻም ወደ ሆቴላቸው ተመልሰው ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።

Day 8
ስምንተኛ ቀን፡ ማክሰኞ ሚያዝያ 13 2012 ዓ.ም./ኤፕሪል 21 2020፣

ተጓዦች ቁርስ ከተመገቡ በኋላ የኢየሩሳሌም ሆቴል ክፍሎቻቸውን አስረክበው ወደ ኢያሪኮ በማቅናት ገዳመ ቆረንጦስን፣ የኤልሣ ምንጭን፣ የዘኬዎስ ዛፍን ይጎበኛሉ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የኢያሪኮ ገብርኤል ገዳም ፀሎት ያደርጉና የምሳ እረፍት ያደርጋሉ፣ የሙት ባሕርን ጨምሮ ቁምራንና አካባቢውን ይጎበኛሉ፣ ከዚያም ወደ ጥብርያዶስ/ገሊላ ባህር ያቀናሉ፣ የሆቴል ክፍሎቻቸውን ይረከባሉ፣ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም በገሊላ ባህር አቅራቢያ በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።

Day 9
ዘጠነኛ ቀን፡ ረቡዕ ሚያዝያ 14 2012 ዓ.ም./ኤፕሪል 22 2020፣

ተጓዦች በጠዋት ተነስተው በዮርዳኖስ ወንዝ ይጠመቃሉ፣ ከቁርስ በኋላ የጀልባ ጉዞ በገሊላ ባህር ላይ ያደርጋሉ፣ የአንቀፀ ብፁዓን ስብከት ተራራን፣ ጌታ 3 አሳና 5 እንጀራ አበርክቶ ያበላበትን ቅዱስ ስፍራ ይጎበኙና በገሊላ ባህር አጠገብ ምሳ ይመገባሉ፣ ጥብርያዶስን፣ ቅፍርናሆምን ጎብኝተው ወደ ሆቴል ይመለሳሉ፣ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም በገሊላ ባህር አቅራቢያ በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።

Day 10
አስረኛ ቀን፡ ሐሙስ ሚያዝያ 15 2012 ዓ.ም./ኤፕሪል 23 2020፣

ተጓዦች ቁርስ ይመገባሉ፣ ከዚያም ደብረ ታቦርን፣ ናዝሬትንና ቃና ዘገሊላን ጎብኝተው የምሳ ዕረፍት ያደርጋሉ፣ ብስራተ ገብኤልንና የእመቤታችንን ምንጭ ጨምሮ የአካባቢውን አብያተ ክርስቲያናት ይጎበኛሉ፣ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም በገሊላ ባህር አቅራቢያ በሚገኘው ሆቴል ይሆናል፡፡

Day 11
አስራ አንደኛ ቀን፡ አርብ ሚያዝያ 16 2012 ዓ.ም./ኤፕሪል 24 2020፣

ተጓዦች ቁርስ ይመገባሉ፣ በመቀጠልም የቀርሜሎስ ተራራን፣ የኤልያስ ዋሻን፣ ኢዮጴን፣ ልዳ ጊዮርጊስን ይጎበኛሉ፣ የመልስ ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም ያደርጋሉ፣ የሆቴል ክፍሎቻቸውን ይረከባሉ፣ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።

Day 12
አስራ ሁለተኛ ቀን፡ ቅዳሜ ሚያዝያ 17 2012 ዓ.ም./ኤፕሪል 25 2020

በሆቴል ቁርስ ይመገባሉ፣ አላዛርን ጎብኝተው በዚያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስትያን ፀሎት አድርገው የምሳ ዕረፍት ያደርጋሉ፣ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው የዕረፍትና የስጦታ እቃዎች የሚገዙበት ጊዜ ይሆናል፣ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።

Day 13
አስራ ሶስተኛ ቀን፡ እሁድ ሚያዝያ 18 2012 ዓ.ም./ኤፕሪል 26 2020፣

ተጓዦች በለሊት ወደ በደብረ ገነት ኪዳነ ምህረት ገዳም የዳግማይ ትንሳኤ በዓል ሥርዓተ ቅዳሴ ላይ ይሳተፋሉ፣ ከዚያም ወደ ሆቴል ተመልሰው ቁርስ ይመገባሉ፣ ለመልስ ጉዞ ዝግጅት ያደርጋሉ፣ ከዚያም የሆቴል ክፍሎችን አስረክበው ምሳ ይመገባሉ፣ በተዘጋጀላቸው አውቶቢስ በመሆን ወደ አየር ማረፊያ ይጓዛሉ።

Day 14
አስራ አራተኛ ቀን፡ ሰኞ ሚያዝያ 19 2012 ዓ.ም./ኤፕሪል 27 2020፣

ተጓዦች ንጋት ላይ አዲስ አበባ ይደርሳሉ፣

ማስታወሻ፡- ይህ የጉብኝት ፕሮግራም ጊዜያዊ መሆኑን እንዲረዱ እንጠይቃለን፣ በሚጎበኙ ቦታዎች በሚኖሩ ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ በመመርኮዝ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተገቢ ለውጦች ሊያደረግበት ይችላል፣ ይህንንም በወቅቱ እናሳውቅቆታለን::

የዋጋ ዝርዝር፣

  • የቪዛ፣ የጉዞ ኢንሹራንስና የመመዝገቢያ 2,500.00 ብር፣
  • የደርሶ መልስ የበረራ ትኬት (አዲስ-ቴልአቪቭ-አዲስ)፣ በወቅቱ በሚኖረው ዋጋ የሚወሰን፣
  • በኢየሩሳም የጉብኝት አገልግሎት ዋጋ በሰው ከ1,950.00 ዶላር ጀምሮ (ጭማሪ ሊኖረው ይችላል)፣
  • በጉብኝት ፓኬጅ ዋጋው የተካተቱ፡- ደረጃ የጠበቁ ባለ4 ኮከብ የማረፊያ ሆቴሎች፣ ቁርስ፣ ምሳ፣ እራት፣ የዘመናዊ አውቶቢስ መጓጓዣ ትራንስፖርት፣ የስብከተ ወንጌል መምህርና አስጎብኚዎች፣ የሚጎበኙ ቦታዎች የመግቢያ ክፍያ፣ የመጠመቂያ ልብስ፣ የፀበል መቅጃ ኮዳ፣

በፓኬጅ ዋጋው ያልተካተተ፡-

  • የአስጎብኚዎችና የሹፌሮች ጉርሻ/ቲፕ፣

You can send your enquiry via the form below.

ትንሳዔ በቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም