የቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም መንፈሳዊ ጉብኝት፣
ከጥንት ከንግሥተ ሳባ ዘመን ጅምሮ እስከ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ዘመን ድረስ፣ ከዚያም አልፎ እስከ አሁን አባቶቻችን ሲያደርጉ እንደቆዩት ታሪካዊቷን ቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም በመሳለም መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በሥጋ በተገለጠበት ወራት በሔደበት ጎዳና ተመላለሰው፣ የረገጠውን መሬት ረግጠውና ሌሎች መካነ ቅዱሳትን ጎብኝተው ትምህርትና በረከትን አግኝተው ይመለሱ፣
ይህንን ጥንታዊና የተቀደሰ ጉዞ ለመስቀል፣ ለልደት/ለገና፣ ለደብረዘይት፣ ለትንሳዔ፣ ለዕርገት እና ለፍለሰታ በዓላት ባለን ሰፊ ልምድና እውቀት ከልብ ከሆነ አገልግሎት ጋር እርሶም ሆኑ ወላጆችዎ ከእኛ ጋር እንዲጓዙ ግብዣ ስናቀርብልዎ ከታላቅ ደስታ ጋር ነው፣

ተጓዦች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ጉዞ ወደ ቴል አቪቭ ያደርጋሉ፣ አመሻሽ ላይ ቴል አቪቭ ይደርሱና አስፈላጊውን የኢሜግሬሽን ሥርዓት ፈፅመው በተዘጋጁት አውቶብሶች ውስጥ ሆነው ወደ ኢየሩሳሌም ያቀናሉ፣ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ የሆቴል ክፍሎቻቸውን ይረከባሉ፡፡ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።

በዚህ ቀን በተያዘው የጉብኝት መርሃ ግብር መሰረት ተጓዥ ምእመናን ከቤተ ሳይዳ ጉብኝታቸውን በመጀመር ለ38 ዓመት በአልጋ ላይ የነበረዉ መጻጉ ወደ ተፈወሰበት ቦታ በመሄድ የመጠመቂያውን ቦታ እና በቅድስት ሐና ስም የታነጸውን ቤተመቅደስ ይጎብኛሉ፣

የአሥራ አራቱን ፍኖተ መስቀሎች ጉብኝት እስከ ዘጠነኛው ምዕራፍ ድረስ ማብራሪያና ትምህርት እየተሰጣቸው ጎብኝተው በመቀጠልም ጌታ የተገነዘበትን፣ የተሰቀለበትን (ቀራንዮ)፣ የተቀበረበትን ቦታ (ጎለጎታ) ይሳለማሉ፣ የምሳ እረፍት ያደርጋሉ፣

ከዚያም ወደ ሆቴላቸው ተመልሰው ዕረፍትና ለማታ ፀሎት ዝግጅት ያደርጋሉ፣ ወደ ቤቴልሄም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኢየሱስ ገዳም ለፀሎት ይሄዳሉ፣ ስርዓተ ቅዳሴ ሲያበቃ ወደ ሆቴል ተመልሰው እረፍት ያደርጋሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።

ተጓዦች በሆቴል ቁርስ ተመገበው እስከ እኩለ ቀን እረፍት ያደረጋሉ፣ ከዚያም የበዓል ምሳ ይመገባሉ፣

በመቀጠልም ጌታ በሐዋርያት መካከል በክብር ወደ ሰማይ ያረገበትን ቅዱስ ስፍራ፣ ከዚያም ሐዋሪያቶች ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት ብለው እንዲጸልዩ በጠየቁት መሰረት አባታችን ሆይ የሚለውን ጸሎት ያስተማረበትን ቅዱስ ስፍራና ጌታ ያድርበት የነበረበትን የኤሌዎንን ዋሻ ይጎበኛሉ፣

ከዚያም ሙሉ የኢየሩሳሌም ከተማን በሚያሳየው ሰበን አርክ አደባባይ በመገኘት ስለጥንቷ የዳዊት ከተማ፣ የሞሪያ ተራራ፣ ጌታ ስለ ኢየሩሳሌም መፍረስ ያለቀሰበትን ቦታ ይጎበኛሉ፣

ወደ ጌቴሰማኒ በመውረድ ጌታችን የጸለየበትን የአታክልቱን ቦታ፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የመቃብር እና በክብር ያረገችበትን ቅዱስ ስፍራ ጎብኝተው፣ የዳዊት መቃብርን፣ ቤተ ፋጌን እና ጌታ የመጨረሻ እራት ያበላበትን ቦታዎች ይጎበኛሉ፣ በዚህም የዕለቱ ጉብኝት ያበቃል፣ ወደ ሆቴል ይመለሳሉ፣ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።

ይህ ቀን ተጓዦች ኢየሩሳሌምን በመልቀቅ ለሁለት ቀናት በናዝሬትና በአካባቢው የሚቆዩበት ቀን ነው፣

ስለሆነም ጠዋት ከቁርስ በኋላ የኢየሩሳሌም ሆቴል ክፍሎቻቸውን አስረክበው ጉዞ ወደ ጥብርያዶስ ያደርጋሉ፣ በመንገዳቸው ላይም በኢያሪኮ በመገኘት በተራራ አናት ላይ የሚገኘውንና ጌታ አርባ ቀን አርባ ለሊት የፆመበትንና የፀለየበትን ገዳመ ቆረንጦስን ይሳለማሉ፣

ከዚያም የኤልሣ ምንጭን ጎብኝተውንና ፀበል ተረጭተው ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የኢያሪኮ ገብርኤል ገዳም በማቅናት ፀሎት ያደርጋሉ፣ ከዚያም የዘኬዎስ ዛፍን ተመልክተው የምሳ እረፍት ያደርጋሉ፣ የሙት ባሕርንና አካባቢውን ጎብኝተው ወደ ናዝሬት በማቅናት የሆቴል ማረፊያ ክፍሎቻቸውን ይረከቡና እረፍት ያደርጋሉ፣ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም ናዝሬት በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።

ተጓዦች በጠዋት ተነስተው የተዘጋጀላቸውን የመጠመቂየ ልብስ ተረክበው በዮርዳኖስ ወንዝ ተምሳሌታዊ ጥምቀት ያደርጋሉ፣ ጉብኝታቸውንም በመቀጠል የአንቀፀ ብፁዓን ስብከት ተራራ ይጎበኛሉ፣ ከዚያም ጌታ 3 አሳና 5 እንጀራ አበርክቶ ያበላበትን ቅዱስ ስፍራ ይጎበኛሉ፣

ወደ ቅፍርናሆም በማቅናት ጌታችን ያስተምርበት የነበረውን የአይሁድ ቤተ ምኩራብ፣ የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ፣ የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ፣ የቀራጩ የማቴዎስ ጨምሮ ሌሎችም ሃዋርያት ለአገልግሎት የተጠሩበትን ቦታዎችና ጌታ ይኖርበት የነበረውን የቅፍርናሆም መንደር ፍርስራሽ ይጎበኛሉ፣

በመቀጠልም በገሊላ ባህር አጠገብ ልዩ የአሳ ምሳ ተመግበውና ተምሳሌታዊ የጀልባ ጉዞ በገሊላ ባህር ላይ አድርገው የዕለቱ ጉብኝት ያበቃል፣ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም ናዝሬት በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።

ተጓዦች ቁርስ በሆቴል ተመግበው የእመቤታችንን ምንጭ ጎብኝተውና ጸበል ቀድተው ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታን እንደምትፀንስ ያበሰራትን ቅዱስ ስፍራ ጎበኝተው ወደ ቃና ዘገሊላ አቅንተው የሰርግ ቤቱን ይጎበኛሉ፣

የምሳ ዕረፍት አድርገው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባህርየ መለኮቱን በገለፀበት የደብረ ታቦር ተራራ ተገኝተውና ፀሎት አድርገው የመልስ ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም ያደርጋሉ፣ የሆቴል ክፍሎቻቸውን ተረክበው ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም በገሊላ ባህር አቅራቢያ በሚገኘው ሆቴል ይሆናል፡፡

ተጓዦች ቁርስ በሆቴል ይመገባሉ፣ በዚህ ቀን ተጓዥ ምዕመናን ወደ ቤቴልሔም በማቅናት ጌታችን የተወለደበትን ዋሻ ከተሳለሙ በኋላ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኢየሱስ ገዳም ፀሎት ያደርጋሉ፣ በመቀጠልም ሄሮድስ ህፃኑን ሊገድል በፈለገ ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል ለቅዱስ ዮሴፍና ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ህፃኑን ይዘው እንዲሸሽ እስከነገረው ሰዓት ድረስ የቆዩበትን የወተት ዋሻ በመባል የሚጠራውን ቅዱስ ስፍራ ይጎበኛሉ፣

በመቀጠል የጌታ መልአክ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም እንደተወለደ የምሥራቹን ለእረኞቹ ወደ አበሰረበትና ኖሎት ተብሎ የሚጠራውን የእረኞች መንደር ይጎበኙና የምሳ እረፍት ያደርጋሉ፣

በመቀጠል ወደ አይንከርም በመሄድ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የተወለደበትንና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ኤልሳቤጥን ልትጠይቃት በሄደችበት ጊዜ እመቤታችንና ኤልሳቤጥ ተገናኝተው ሰላምታ የተለዋወጡበትን ገዳም ይጎበኛሉ፣

ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው በመንገዳቸው ላይ ጌታችን ከኤማሁስ መንገደኞች ከሉቃስና ቀልዮጳ ጋር ተገናኝቶ ህብስትን ባርኮ ያበለባትን ቅዱስ ሥፍራ ይጎበኛሉ፣

ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው የዕረፍትና የስጦታ እቃዎች የሚገዙበት ጊዜ ይሆናል፣ ለመልስ ጉዞ ዝግጅት ያደርጋሉ፣ ዕራት በሆቴል ይመገባሉ፣ አዳርም ኢየሩሳሌም በሚገኘው ሆቴል ይሆናል።

በሆቴል ቁርስ ይመገባሉ፣ ከዚያም የሆቴል ክፍሎችን አስረክበው በተዘጋጀላቸው አውቶቢስ በመሆን ወደ አየር ማረፊያ ይጓዛሉ። ተጓዦች ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ይደርሳሉ፣

ማስታወሻ፡- ይህ የጉብኝት ፕሮግራም ጊዜያዊ መሆኑን እንዲረዱ እንጠይቃለን፣ በሚጎበኙ ቦታዎች በሚኖሩ ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ በመመርኮዝ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተገቢ ለውጦች ሊያደረግበት ይችላል፣ ይህንንም በወቅቱ እናሳውቅቆታለን::

የዋጋ ዝርዝር፣
- የቪዛ፣ የጉዞ ኢንሹራንስና የመመዝገቢያ 2,500.00 ብር፣
- የደርሶ መልስ የበረራ ትኬት (አዲስ-ቴልአቪቭ-አዲስ)፣ በወቅቱ በሚኖረው ዋጋ የሚወሰን፣
- በኢየሩሳም የጉብኝት አገልግሎት ዋጋ በሰው ከ1,150.00 ዶላር ጀምሮ (ጭማሪ ሊኖረው ይችላል)፣
- በጉብኝት ፓኬጅ ዋጋው የተካተቱ፡- ደረጃ የጠበቁ ባለ4 ኮከብ የማረፊያ ሆቴሎች፣ ቁርስ፣ ምሳ፣ እራት፣ የዘመናዊ አውቶቢስ መጓጓዣ ትራንስፖርት፣ የስብከተ ወንጌል መምህርና አስጎብኚዎች፣ የሚጎበኙ ቦታዎች የመግቢያ ክፍያ፣ የመጠመቂያ ልብስ፣ የፀበል መቅጃ ኮዳ፣
በጉብኝት ፓኬጅ ዋጋው ያልተካተተ
- የአስጎብኚዎችና የሹፌሮች ጉርሻ/ቲፕ፣